በአፍሪካ ዋንጫ ግብጽ ዚምባቡዌን አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
በአፍሪካ ዋንጫ ግብጽ ዚምባቡዌን አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 13/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት ሁለተኛ ጨዋታ ግብጽ ዚምባቡዌን 2 ለ 1 አሸንፋለች።
ማምሻውን በጋዲር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፕሪንስ ዱቤ በ20ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ዚምባቡዌን መሪ አድርጓል።
ከእረፍት መልስ ኦማር ማርሙሽ በ64ኛው ደቂቃ ላይ በግሩም ሁኔታ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ጎል ግብጽ አቻ ሆናለች።
መሐመድ ሳላህ በ91ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ግብጽ ማሸነፍ ችላለች።
በጨዋታው ግብጽ በተጋጣሚዋ ላይ ከፍተኛ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች።
ዚምባቡዌ የተደራጀ መከላከል እና የፈጣን መልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴዋ ነጥብ ሊያስገኝላት አልቻለም።
ውጤቱን ተከትሎ የሰባት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ግብጽ ሶስት ነጥብ አግኝታለች።
በዚሁ ምድብ ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ አንጎላን 2 ለ 1 አሸንፋለች።
የምድቡ ሁለተኛ መርሃ ግብር ታህሳስ 17 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ግብጽ ከደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
አንጎላ ከዚምባቡዌ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።