ቀጥታ፡

አስቶንቪላ ማንችስተር ዩናይትድን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 12/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አስቶንቪላ ማንችስተር ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሞርጋን ሮጀርስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።

ማትያስ ኩንያ ለዩናይትድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በጨዋታው ላይ የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ በጉዳት ምክንያት በእረፍት ሰዓት በሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ተቀይሮ ወጥቷል።

በሊጉ ሰባተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው አስቶንቪላ በ36 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንችስተር ዩናይትድ በ26 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ነገ ፉልሃም እና ኖቲንግሃም ፎረስት በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም