ቀጥታ፡

ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 12/2018 (ኢዜአ)፡- ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ አቻ በመለያየት ነጥብ ተጋርተዋል።

በ10ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተገናኙት ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ ጨዋታቸውን አድርገዋል።

በጨዋታው ላይ በ27ኛው ደቂቃ ፍጹም ጥላሁን በራስ ላይ ባስቆጠራት ግብ ሲዳማ ቡና ሲመራ ቢቆይም፤ ሀብታሙ ጉልላት በ90ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

በተመሳሳይ ሠዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም መቻል ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።


 

ቀደም ብሎ 7 ሠዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ የዛሬ መርሐ-ግብር ድሬዳዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በዚህ ጨዋታ ያሬድ ታደሰ በ27ኛው ደቂቃ እንዲሁም ነቢል ኑሪ በ30ኛው ደቂቃ ግቦቹን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም