ቀጥታ፡

ድሬዳዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 12/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያሬድ ታደሰ በ27ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ጎል ድሬዳዋ ከተማ መሪ ሆኗል።

ብዙም ሳይቆይ ነቢል ኑሪ በ30ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል አዳማ ከተማን አቻ አድርጓል።

ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በ13 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 11 ከፍ አድርጓል።

አዳማ ከተማ በ17 ነጥብ ከነበረበት አምስተኛ ደረጃ ወደ አራተኛ ከፍ ብሏል።

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ መቻል ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተመሳሳይ ከቀኑ 10 ሰዓት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም