ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ አስቶንቪላ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ይጫወታሉ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 12/2018(ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በአስቶንቪላ እና ማንችስተር ዩናይትድ መካከል ዛሬ ይደረጋል።

ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ በቪላ ፓርክ ስታዲየም ይካሄዳል።

አስቶንቪላ በ33 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ማንችስተር ዩናይትድ በ26 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። 

ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ61ኛ ጊዜ ነው። 

ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 60 ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ  41 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ አስቶንቪላ 5 ጊዜ ድል ቀንቶታል። በቀሪ 14 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

በ60ዎቹ ጨዋታዎች ላይ ማንችስተር ዩናይትድ 108 ግቦችን ሲያስቆጥር  አስቶንቪላ  በበኩሉ 40 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች በነበራቸው ግንኙነት ማንችስተር ዩናይትድ ስድስት ጊዜ ሲያሸንፍ አስቶንቪላ ደግሞ በሁለት ጨዋታዎች ድል ቀንቶታል።  ሁለት ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። 

አስቶንቪላ ዛሬ ካሸነፈ በሊጉ ሰባተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘግባል።  በአንጻሩ ማንችስተር ዩናይትድ ሶስት ነጥብ ካገኘ ደረጃውን ያሻሽላል። 

የ40 ዓመቱ ማይክል ኦሊቨር ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም