ቀጥታ፡

አርሰናል ኤቨርተንን በማሸነፍ ወደ ሊጉ መሪነት ተመለሰ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ኤቨርተንን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቪክቶር ዮኮሬሽ በ27ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ግብ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

አርሰናል በጨዋታው በኳስ ቁጥጥር እና ግልፅ የግብ እድሎችን በመፍጠር ከተጋጣሚው ተሽሎ ተገኝቷል።

በውድድር ዓመቱ 12ኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ39 ነጥብ ለሰዓታት አጥቶት የነበረውን የሊጉን መሪነት መልሶ አግኝቷል።

በአንጻሩ በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኤቨርተን በ24 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።

ማምሻውን በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን 4 ለ 1 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም