ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው - ኢዜአ አማርኛ
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው ሲሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው።
ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል ሲሉ አንስተዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለጹት አንድ ሺህ ሰለሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆነዋል ነው ያሉት።
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ከተሞች ይደርሳል ብለዋል።
በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲሉም አረጋግጠዋል።