ቀጥታ፡

በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በሳይበር ደህንነት ላይ በርካታ አስቻይ መሰረቶች ተጥለዋል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በሳይበር ደህንነት ላይ በርካታ አስቻይ መሰረቶች ተጥለዋል ሲሉ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

በመድረኩ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በሳይበር ደህንነት ላይ በርካታ አስቻይ መሰረቶች ተጥለዋል ነው ያሉት።

በዚህም የራሳችንን ክላውድ መሰረተ ልማት በመገንባት በኢትዮጵያ የዲጂታል አገልግሎት መተማመን መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

ለጸጥታ ተቋማትም የዲጂታል ፎረንሲክ ላብ በመገንባት ወደ ስራ እንዲገባ መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የሳይበር ደህንነት ስትራቴጂካዊ ትኩረት ተሰጥቶታል ሲሉም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

በዚህም የማይበገር ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማት መገንባት፣ የህዝብ መሰረተ ልማትን ማዘመን፣ የአደጋ ምላሽ መስጫ ማዕከል የማቋቋምና የግል ተቋማትን ያካተተ የሳይበር ደህንነት ስራ እንዲጎለብት ይሰራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም