ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ላይ ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተተግብሯል። - ኢዜአ አማርኛ
ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ላይ ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተተግብሯል።
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ላይ ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተተግብሯል ሲሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ ዮዳሄ አርአያስለሴ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
በመድረኩ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ ዮዳሄ አርአያስለሴ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ላይ ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተተግብሯል ብለዋል።
አሁን ላይ 30 ሚሊዮን ዜጎች ፋይዳ መታወቂያ ተመዝግበዋል ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል።
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ላይ ፋይዳ ስትራቴጂካዊ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ የማድረግ ስራም ይሰራል ነው ያሉት።
በተለይ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያሉ አገልግሎቶችን ከፋይዳ ጋር በማስተሳሰር በስትራቴጂው የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ ሁሉም በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ አቶ ዮዳሄ አርአያስለሴ አስገንዝበዋል።