በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስነ ምህዳር ማስፋት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ይከናወናሉ - ኢዜአ አማርኛ
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስነ ምህዳር ማስፋት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ይከናወናሉ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስነ ምህዳር ማስፋት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ይከናወናሉ ሲሉ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስነ ምህዳር ማስፋት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል።
የራሳችንን ክላውድ ከመጠቀም ባሻገር ውጤታማ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ይደረጋል ሲሉም ገልጸዋል።
በዚህም በተደራጀ አግባብ መረጃዎች ለወሳኔ አሰጣጥ እንዲውሉ የሚሰራ ሲሆን፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ገለልተኛ ብሔራዊ የመረጃ ባለስልጣን ወደ ስራ እንዲገባ ይደረጋል ነወ ያሉት።
ዲጂታል አገልግሎት አሰጣጦችን የማናበብንና ወጥ የማድረግ ስራ ላይም ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረዋል።