በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የንግድ ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች ይከናወናሉ - ኢዜአ አማርኛ
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የንግድ ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች ይከናወናሉ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የንግድ ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ይድነቃቸው ወርቁ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
በመድረኩ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ይድነቃቸው ወርቁ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የንግድ ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል።
በተለይ የሀገር ውስጥ የኢ-ኮሜርስ ስርዓትንና የንግድ ስራ የሚውሉ ሎጂስቲክስን በማሟላት የንግድ ሰርዓቱ ይበልጥ እንዲሳለጥ ይሰራል ነው ያሉት።
የወጪና ገቢ ንግድ ላይ ያሉ አሰራሮችንም ዲጂታል እንዲሆኑ በማድረግ ዘርፉ ለኢኮኖሚ ያለውን ፋይዳ ይበልጥ እንዲጎለብት ይደረጋል ሲሉም አረጋግጠዋል።