ቀጥታ፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በሲቪል ምዝገባና የዜግነት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በሲቪል ምዝገባና የዜግነት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል ሲሉ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) በተገኙበት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ እንዳሉት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በሲቪል ምዝገባና የዜግነት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል

 አክለውም አግልግሎቱን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ረገድም ትልቅ ተሞክሮ የሚሆን ስራ ተከናወኗል ብለዋል።

ለአብነትም በአዲስ አበባ ከማዕከል እስከ ወረዳ ትስስር መፍጠር የተቻለ ሲሆን፣ ለስራው የሚያገለግሉ መተግበሪያዎችም በሀገር ውስጥ አቅም የለሙ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

በዚህም የቤተሰብ ምዝገባ፣ ወሳኝ ኩነት፣የነዋሪዎች አገልግሎትና የማረጋገጥ ስራዎች በዲጂታል ስርዓት ተግባራዊ እየተደረጉ ነው ብለዋል።

ይህም 2030 ተቋማት በዲጂታል አሰራርና በመረጃ የተሳሰሩ እንዲሆኑ ለሚከናወነው ስራ ተሞክሮ መሆን የሚችል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም