ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ታክስ የመሰብሰብ አቅም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አምጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ታክስ የመሰብሰብ አቅም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አምጥቷል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ታክስ የመሰብሰብ አቅም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አምጥቷል ሲሉ የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ዳዊት ውብሸት አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
በመድረኩ የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ዳዊት ውብሸት እንደገለጹት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ታክስ የመሰብሰብ አቅም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አምጥቷል።
አክለውም አሁን ላይ 58 ሺህ የሚሆኑ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በዲጂታል ስርዓት አማካኝነት እያሳወቁ ይገኛሉ ብለዋል።
በቀጣይም በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አማካኝነት ከተቋማት ጋር ተናባቢና ተመጋጋቢ የዲጂታል ስርዓትን በማጠናከር ታክስ የመሰብሰብ አቅምን ይበልጥ እንዲጠናከር ይሰራል ነው ያሉት።