ቀጥታ፡

ሊቨርፑል ቶተንሃም ሆትስፐርስን አሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሊቨርፑል ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 1 አሸንፏል።  

ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አሌክሳንደር ኢሳቅ እና ሁጎ ኢኪቲኬ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ሪቻርልሰን ለቶተንሃም ሆትስፐርስ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የቶተንሃሞቹ ዣቪ ሲመንስ እና ክሪስቲያን ሮሜሮ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል። 

በሊጉ ዘጠነኛ ድሉን ያስመዘገበው ሊቨርፑል በ29 ነጥብ ደረጃውን ወደ አምስተኛ ከፍ አድርጓል። 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ22 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም