ሃዋሳ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አምበሉ ጌታነህ ከበደ እና ያሬድ ብሩክ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
አማኑኤል ኤርቦ ለኢትዮጵያ መድን ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ አምስተኛ ድሉን ያሳካው ሃዋሳ ከተማ በ17 ነጥብ ደረጃውን ከሰባተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ መድን በ12 ነጥብ ከነበረበት 16ኛ ደረጃ ወደ 17 ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ገብቷል።