ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቴዎድሮስ ታፈሰ እና ኪዳኔ አሰፋ በጨዋታ፣ መልካሙ ቦጋለ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሙአዝ ጋሊ ለሸገር ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ ሁለተኛውን ድል ያስመዘገበው ወላይታ ድቻ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 15ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሸገር ከተማ በ12 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።