ቀጥታ፡

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ኢትዮጵያ ቡና አንድ አቻ ተለያይተዋል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘላለም አባተ በ10ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ኢትዮጵያ ቡናን መሪ አድርጓል።

ኪሩቤል ወንድሙ በ19ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፋት ጎል ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ሆኗል። 

ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በስምንት ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። 

ኢትዮጵያ ቡና በ12 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም