ቀጥታ፡

ኒውካስትል ዩናይትድ እና ቼልሲ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 11/2018 (ኢዜአ)፦በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ እና ቼልሲ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

በሴንት ጀምስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኒክ ዎልትሜድ በአራተኛው እና 20ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ጎሎች ኒውካስትል ዩናይትድ መምራት ችሎ ነበር።

ከእረፍት መልስ ሪስ ጀምስ በ49ኛው እና ጆአኦ ፔድሮ በ66ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ግቦች ቼልሲ አንድ ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ29 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በ23 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም