ፍትህ ወልደሰንበት (ዶ/ር) የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን አምስት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ - ኢዜአ አማርኛ
ፍትህ ወልደሰንበት (ዶ/ር) የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን አምስት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፍትህ ወልደሰንበት (ዶ/ር) የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን አምስት ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል።
የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን አምስት ስብስባ በግብጽ ካይሮ ተካሄዷል።
በስብሰባው ላይ የዞን አምስት አባል ሀገራት ፍትህ ወልደሰንበት (ዶ/ር) የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን አምስት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በድጋሚ መርጠዋቸዋል።
ፍትህ ወልደሰንበት (ዶ/ር) የአባል ሀገራቱን ሙሉ ድጋፍ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።
ፕሬዝዳንቱ ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት ይመራሉ።
ፍትህ ወልደሰንበት (ዶ/ር) እ.አ.አ 2021 አንስቶ ኮንፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት እያገለገሉ ይገኛል።
ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ብሩንዲ፣ ጅቡቲ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳ፣ ሶማሊያ እና ግብጽ የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን አምስት አባል ሀገራት ናቸው።