ቀጥታ፡

በሶማሌ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጀመረ

ጅግጅጋ፤ ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ)፡- በሶማሌ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ዜጎች በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአንድ ቦታ በርካታ አገልግሎቶችን የሚያገኙበት ዘመናዊ አሰራር መሆኑ ይታወቃል።

በዛሬው እለትም በሶማሌ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጀምሯል።

አገልግሎቱንም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሃመድ እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አክሊሉ ታደሰ አስጀምረውታል።

በጅግጅጋ ከተማ የተገነባው ማዕከሉ በመጀመሪያ ምዕራፍ በ9 ተቋማት 32 አገልግሎቶችን አቀናጅቶ የሚሰጥ መሆኑም ታውቋል።

የሶማሌ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እነዚህን አገልግሎቶች በተቀናጀ መንገድ መስጠት በሚያስችል መልኩ በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ ወደ ስራ መግባቱም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም