ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል ከኤቨርተን ማንችስተር ሲቲ ከዌስትሃም ዩናይትድ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 11/2018(ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል።

የገና ሰሞን ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ።

ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ኤቨርተን ከአርሰናል በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም ይጫወታሉ።

ኤቨርተን በ24 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። አርሰናል በ36 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው።

በኢትሃድ ስታዲየም ማንችስተር ሲቲ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ምሽት 12 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።


ማንችስተር ሲቲ በ34 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ዌስትሃም ዩናይትድ በ13 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ሁለቱ ጨዋታዎች በዋንጫ ፉክክሩ ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው።

በሌሎች መርሃ ግብሮች ኒውካስትል ዩናይትድ ከቼልሲ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ጋር ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

ዎልቭስ ከብሬንትፎርድ፣ ብራይተን ከሰንደርላንድ እና ቦርንማውዝ ከበርንሌይ በተመሳሳይ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

ሊድስ ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ጨዋታዎች ያደርጋሉ።

የፈረንጆች ገና ሰሞን ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ የሚካሄዱ ሲሆን በቀጣይ 16 ቀናት የአራት ሳምንታት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም