ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ተደርጓል። 

ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በ27 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት በ26  ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። 

ዛሬ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ ከተስተካካይ መርሃ ግብር ውጪ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መጀመሪያ ዙር ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሸገር ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተስተካካይ ጨዋታዎቹን በቀጣይ የሚያደርግ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም