ቀጥታ፡

 የፋይዳ መታወቂያ አገልግሎት ተደራሽነት ቀልጣፋ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ሆነናል-ተገልጋዮች

ሀዋሳ፤ ታህሳስ 10/2018 (ኢዜአ)፦ በሀዋሳ ከተማ የፋይዳ መታወቂያ አገልግሎት ተደራሽነት ቀልጣፋ በመሆኑ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ተገልጋዮች ገለጹ።

ኢዜአ በሀዋሳ ያነጋገራቸው ተገልጋዮች እንዳሉት፤ በከተማዋ የፋይዳ መታወቂያ አገልግሎት ተደራሽነት ቀልጣፋ በመሆኑ የፋይዳ መታወቂያ ይዘው በሚሄዱባቸው አገልግሎት መስጫ ተቋማት ያለ እንግልት መስተናገድ ችለዋል።

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሄዋን ብርሀኑ እንዳሉት፤ ፋይዳ መታወቂያ ባለመያዛቸው ምክንያት አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ሲቸገሩ እንደቆዩ ተናግረዋል።


 

አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ኢትዮ ቴሌኮም በመምጣት በፍጥነት መስተናገዳቸውን ገልጸዋል።

ተማሪ ውብሼ ሀብቴ እና ወጣት ብሩክ ሺመልስ ፤ባገኙት ፈጣን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው ፋይዳ መታወቂያ መያዝ  ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ብለዋል።


 

በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅን የፋይዳ መታወቂያ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ተድላ ሺመልስ እንዳሉት፤ ቀደም ሲል ስለ ፋይዳ ግንዛቤ በህብረተሰቡ ዘንድ በበቂ ሁኔታ ባለመኖሩ ምክንያት አገልግሎት ፈላጊዎቸ ቁጥር አነስተኛ ነበር።


 

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግንዛቤ መጨመሩና ተቋማት ለሚሰጡት አገልግሎት ፋይዳ መታወቂያን እንደ ቅድመ ሁኔታ መጠየቅ መጀመራቸው መታወቂያውን ለመውሰድ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ገልጸዋል።

አገልግሎቱም በትምህርት ቤቶች፣ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎችና በገበያ ቦታዎች ጭምር እየተሰጠ እንደሚገኝም አቶ ተድላ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም