ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል። 

ረፋድ ላይ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳግማዊት ሰለሞን እና ዙፋን ደፈርሻ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

በውድድር ዓመቱ 12ተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ36 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።

በአንጻሩ በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ15 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።


 

የኢትዮ ኤሌክትሪኳ አጥቂ ዳግማዊት ሰለሞን በውድድር ዓመቱ ያስቆጠረቻቸውን ግቦች ወደ 18 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቷን አጠናክራለች።

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ሃዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም