ቀጥታ፡

የገቢ እና ወጪ ምርቶችን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ ትኩረት ተደርጓል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና ጅቡቲ የገቢ እና ወጪ ምርቶች ትራንስፖርትን ይበልጥ ለማቀላጠፍ ሀገራቱ ያላቸውን ትሰስር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ጋር ተወያይቷል፡፡


 

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የገቢና ወጪ ምርቶች ትራንስፖርትን ይበልጥ የተቀላጠፈ ለማድረግና ዘርፈ ብዙ ትስስራቸውን አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው በሀገራቱ መካከል ያለውን አጋርነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይም መክረዋል።


 

በአቶ አደም ፋራህ የተመራውና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) እና የኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የልዑካን ቡድን በጅቡቲ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም