ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሸገር ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሰርካለም ባሳ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥራለች።

ሜላት አሊሙዝ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

በሊጉ ዘጠነኛ ድሉን ያስመዘገበው ሸገር ከተማ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ27 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ20 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። 

ዛሬ በተደረገ ሌላኛው መርሃ ግብር መቻል ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም