ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል ድሬዳዋ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል። 

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መዲና አወል ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ቤዛዊት ንጉሴ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች። 

በሊጉ ዘጠነኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ29 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ13 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። 

ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከቦሌ ክፍለ ከተማ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም