ቀጥታ፡

አሰራሮችን ዲጂታላይዝ በማድረግ የጀመርናቸውን ስራዎች ማስቀጠል የሚያስችለን አቅም ፈጥረናል

ሰመራ፣ ታህሳስ 9/2018(ኢዜአ):- አሰራሮችን ዲጂታላይዝ በማድረግ የተጀመሩትን ሥራዎች ማስቀጠል የሚያስችል አቅም መፍጠራቸውን የብልፅግና ፓርቲ  አመራሮች ተናገሩ።

በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት ስርዓት የዲጂታል ብልፅግና አተገባበር  አውቶሜሽን ላይ ለአመራሮች ያዘጋጀው  ስልጠና በሰመራ መሰጠቱ ይታወሳል። 

በሰልጠናው ላይ በብልጽግና ፓርቲ የሁሉም ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች አመራሮች ተሳትፈዋል። 

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ አመራሮች እንዳሉት ስልጠናው በተቋማት የዲጂታል አሰራርን የተከተለ የተናበበና የተቀናጀ ሪፖርት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ግንዛቤ ሰጥቷቸዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስትራተጂክ ስራ አመራርና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብይ አበባው እንዳሉት ለዲጀታል ስራ መሠረታዊ የሆኑ ክህሎቶችና የሰው ኃይልን ከማሟላት ጀምሮ የተከናወኑ ሰፋፊ ተግባራት አሉ።


 

በዚህ ስልጠናም የተጀመሩትን ስራዎች ለማጠናከር በግብአትነት የሚያገለግሉ ግንዛቤዎች ተገኝተዋል ብለዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የስትራተጂክ ስራ አመራርና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አንተነህ አየለ በበኩላቸው ከክልል እሰከ ቀበሌ የሚያስተሳስር ዲጂታል ስርዓት እየተገነባ መሆኑን ገልጸዋል።


 

በዚህ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር እና ልውውጥ ደግሞ ስራዎችን ቀልጣፋና ቀላል ከማድረግ ባሻገር ጊዜና ሃብት መቆጠብ የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ላይ መሆኑን አስረድተዋል።


 

በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስትራቴጂክ ስራ አመራርና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከበደ እንዳሉት በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ከማሟላት ጀምሮ፣ 8 ሶፍትዌሮችን በማበልፀግ ተግባራዊ ማድረግ እንደተቻለ አመልክተዋል።


 

ስልጠና ከሰጡ አመራሮች መካከል የኢትዮጵያ ስታስቲክሰ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ሜሮን ከፈለው (ዶ/ር) እንዳሉት የዲጂታል አሰራር ስራዎችን ለማቀላጠፍ በእጅጉ ያግዛል።

የዲጂታላይዜሽን ስርዓት ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች፣ በየክልሉ እና በየተቋማቱ በእየተሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።



በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀላፊ አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር በበኩላቸው እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ የዲጂታል አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ጊዜና ወጪን በመቆጠብ ባሻገር የኢትዮጵያ ኮደርሰ  ስልጠና ላይ ያለውንም ክፍተት የሚሞላ መሆኑን ጠቅሰዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም