በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ልደታ ክፍለ ከተማ አርባ ምንጭ ከተማን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ልደታ ክፍለ ከተማ አርባ ምንጭ ከተማን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ልደታ ክፍለ ከተማ አርባ ምንጭ ከተማን 4 ለ 2 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሄለን እሸቱ፣ ረድኤት ዳንኤል እና ሰብለወንጌል ወዳጆ በጨዋታ፣ ቃልኪዳን ጥላሁን በፍጹም ቅጣት ምት ለልደታ ክፍለ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
መሰረት ማቴዎስ እና ፍሬህይወት በድሉ ለአርባ ምንጭ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ልደታ ክፍለ ከተማ በስምንት ነጥብ ደረጃውን 13ኛ ወደ 14ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በሊጉ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባ ምንጭ ከተማ በተመሳሳይ ስምንት ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ማለት ወራጅ ቀጠና ገብቷል።
ዛሬ በተደረጉ የ13ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ባህር ዳር ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 0፣ ሲዳማ ቡና ይርጋ ጨፌ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።