ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት በሰላም ግንባታና ግጭትን አስቀድሞ መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ በትብብር ይሰራሉ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት በሰላም ግንባታና ግጭትን አስቀድሞ መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ በትብብር ይሰራሉ
አዲስ አበባ፤ታኅሣስ 8/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት በሰላም ግንባታና ግጭትን አስቀድሞ መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ገለጹ።
የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገር ጋር በሰላም ግንባታና ግጭትን አስቀድሞ መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፤ የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር ስለሚያደርገው ጥረት ገለጻ አድርገዋል።
የአውሮፓ ኅብረት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ እና ገንቢ ሚናም ማድነቃቸውን ሚኒስቴሩ ለኢዜአ የላከው መረጃ አመላክቷል።
አምባሳደሯ በበኩላቸው፥ የተጀመሩ የጋራ ግቦችን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
አክለውም፥ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጉዞ ቀጣይነት ያለው እንዲሁም የተጠናከረ ትብብር ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።