በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ይርጋጨፌ ቡናን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ይርጋጨፌ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና ይርጋ ጨፌ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ምትኬ ብርሃኑ እና ቢታኒያ አስተረፍ የማሸነፊያ ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አዳነች አስፋው ለይርጋ ጨፌ ቡና ብቸኛውን ግብ አስቆጥራለች።
በሊጉ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ18 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ይርጋ ጨፌ ቡና በበኩሉ በ10 ነጥብ ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ወደ 11ኛ ዝቅ ብሏል።
በአሁኑ ሰዓት ልደታ ክፍለ ከተማ ከአርባ ምንጭ ከተማ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።