የኢትዮጵያ እና ህንድ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እና ህንድ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እና ህንድ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ የሁለትዮሽ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ኢትዮጵያን ዳግም እንደሚጎበኙ ተስፋ አለኝ ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ህንድ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ዲፕማሲያዊ ግንኙነት በዘላቂነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።