የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ምክር ቤቱ የድጋፍ፣ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን ያጠናክራል - ኢዜአ አማርኛ
የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ምክር ቤቱ የድጋፍ፣ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን ያጠናክራል
ድሬዳዋ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ምክር ቤቱ የድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ስራውን እንደሚያጠናክር የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ገለጹ።
የአስተዳደሩ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ ዓመት 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ አብዲ ሙክታርን የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አድርጎ መርጧል።
በዚሁ ጊዜ አፈ-ጉባኤው ባደረጉት ንግግር አስፈፃሚው አካል የህዝብ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በፍጥነት፣ በጥራትና በላቀ መልኩ ለመፈፀም መዘጋጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ምክር ቤቱ የድጋፍ፣ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን እንደሚያጠናክርም ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ በዛሬው አስቸኳይ ጉባኤው የቀረቡለትን አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። በዚህም መሠረት፦
1/ ወይዘሮ ሌሊሴ አህመድ - የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
2/ አቶ ብሩክ ወርቅነህ - የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም
3/ አቶ ፉአድ መሐመድ - የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን የተጣለባቸውን የህዝብ ኃላፊነት በታማኝነትና በቁርጠኝነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል።