ባህር ዳር ከተማ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ከተማ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምህረት ታፈሰ እና ትዕግስት ኃይሌ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ባህር ዳር ከተማ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዟል።