ቀጥታ፡

በካራባኦ ዋንጫ ሁለት ለግማሽ ፍጻሜ የሚያልፉ ክለቦች የሚለዩባቸው ጨዋታዎች ይደረጋሉ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ዛሬ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። 

ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ በኢትሃድ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ማንችስተር ሲቲ በአራተኛው ዙር ስዋንሲ ሲቲን 3 ለ 1 ማሸነፉ ይታወቃል።

ተጋጣሚው ብሬንትፎርድ በበኩሉ ግሪምስቢ ታውንን 5 ለ 0 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። 

ማንችስተር ሲቲ የካራባኦ ዋንጫን ስምንት ጊዜ በማንሳት ከስኬታማ ክለቦች ውስጥ የሚጠቀስ ነው። 

ብሬንትፎርድ በውድድር ተሳትፎ ታሪኩ ለፍጻሜ ደርሶ አያውቅም ። 

በሌላኛው መርሃ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ከፉልሃም ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ በሴይንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ኒውካስትል ዩናይትድ በአራተኛው ዙር ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 0 ረቷል። ፉልሃም ዋይኮምብን በመለያት ምት ማሸነፍ ችሏል።

ኒውካስትል የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ነው። ቡድኑ የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ የለንደኑን ተጋጣሚውን ማሸነፍ ይኖርበታል።

ፉልሃም የካራቦ ዋንጫን አንስቶ አያውቅም። 

ትናንት በተደረገ የመጀመሪያ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ቼልሲ ካርዲፍ ሲቲን 3 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ ያለፈ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም