ቀጥታ፡

ቼልሲ ለካራባኦ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ያለፈ የመጀመሪያ ቡድን ሆኗል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 7/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ዋንጫ የመጀመሪያ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር ቼልሲ ካርዲፍ ሲቲን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በካርዲፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኤሌሃንድሮ ጋርናቾ በ57ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ቼልሲ መሪ ሆኗል።

ዴቪድ ተርንቡል በ75ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ካርዲፍ አቻ አድርጓል።

ፔድሮ ኔቶ በ82ኛው ደቂቃ ቼልሲን ሁለተኛውን ጎል  አስቆጥሯል።

ጋርናቾ ለራሱ ሁለተኛውን ለቡድኑ ሶስተኛውን ግብ በ93ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ በጨዋታው አብዛኛውን ቋሚ ተሰላፊዎቹን ተቀያሪ ወንበር ላይ አስቀምጦ የጀመረ ሲሆን ከእረፍት መልስ ተጫዋቾቹን ቀይሮ በማስገባት ውጤት ይዞ ወጥቷል።

በእንግሊዝ ሶስተኛ የሊግ እርከን ሊግ አንድ የሚገኘው የዌልሱ ካርዲፍ ሲቲ ቼልሲን ቢፈትንም ማሸነፍ አልቻለም።

ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ ለካራባኦ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ያለፈ የመጀመሪያ ቡድን ሆኗል።

የካራባኦ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር ነገም ቀጥሎ ሲውል ማንችስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ እና የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ኒውካስትል ዩናይትድ ከፉልሃም ይጫወታሉ።

አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ በዚህ ሳምንት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በመርሃ ግብር መደራረብ ምክንያት ለቀጣዩ ሳምንት ተራዝሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም