ቀጥታ፡

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ትስስር የሚያመለክት ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 7/2018(ኢዜአ)፦ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ትስስር የሚያመለክት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። 

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። 


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ለይፋዊ ጉብኝት በመቀበላቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል። 


 

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮች መካከል እያደገ የመጣውን ትስስር የሚያመለክት እንደሆነ ተናግረዋል። 

ውይይቶቻችን በጋራ የቅድሚያ ጉዳዮቻችን ላይ ትብብሮቻችንን የበለጠ የምናጠናክርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም