ኢትዮጵያ አምስተኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች እንድታዘጋጅ ተመረጠች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ አምስተኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች እንድታዘጋጅ ተመረጠች
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 7/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ አምስተኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።
አራተኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች በአንጎላ ሉዋንዳ እየተካሄደ ይገኛል።
የአፍሪካ ብሔራዊ የኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ከውድድሩ ጎን ለጎን መደበኛ ስብስባውን አድርጓል።
ኢትዮጵያ በስብስባው ላይ አምስተኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች ለማዘጋጀት ያቀረበችው ጥያቄ በአኖካ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሙሉ ድምፅ በማግኘት ተቀባይነት አግኝቷል።
በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ ከሁለት አመት በኋላ የሚደረገውን አምስተኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች እንደምታስተናግድ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።