ቀጥታ፡

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ታህሣሥ 7/2018(ኢዜአ)፦ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ በነገው ዕለት ይካሄዳል።

6ኛው የሁለቱ ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ነገ እንደሚካሄድም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።

በጋራ ስብሰባው የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ምክር ቤቱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም