ቀጥታ፡

ስምንት ግቦች በተቆጠሩበት አዝናኝ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ አቻ ተለያዩ


አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ አራት አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አማድ ዲያሎ፣ ካሲሚሮ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ማትያስ ኩንሃ ለማንችስተር ዩናይትድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አንቶዋን ሴሜንዮ፣ ኢቫኒልሰን፣  ማርከስ ታቫርኒየር እና ጁኒየር ክሩፒ ለቦርንማውዝ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በጨዋታው ሶስት ጊዜ መምራት ቢችልም ውጤቱን ማስጠበቅ አለመቻሉ ዋጋ አስከፍሎታል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ እና አዝናኝ ፉክክር ታይቶበታል። የሁለቱ ቡድኖች የተከላካይ ክፍል መስመር ተጋላጭነትም በግልጽ ለመመልከት ተችሏል።

በጨዋታው ከ30 በላይ የግብ ሙከራዎች ተደርገዋል።

ውጤቱን ተከቶሎ ማንችስተር ዩናይትድ በ26 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ስድስተኛ ከፍ አድርጓል።

ቦርንማውዝ በ21 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 13ኛ ከፍ ማድረግ ችሏል። ቡድኑ ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም