ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ዋንጫ መቀሌ 70 እንደርታ ለሩብ ፍጻሜ አለፈ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የሶስተኛ ዙር የመጨረሻ መርሃ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍጹም ዓለሙ በ28ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ መቀሌ 70 እንደርታ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለ የመጨረሻው ቡድን ሆኗል።

ሲዳማ ቡና፣ ቤንች ማጂ ቡና፣ መቻል፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ቦዲቲ ከተማ፣ ኢትዮጵያ መድን እና ነጌሌ አርሲ ሌሎች የሩብ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦች ናቸው። 

የኢትዮጵያ ዋንጫን የሚያሸንፈው ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ በ1937 ዓ.ም የተጀመረ አንጋፋ የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም