ቀጥታ፡

 የግብርና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2018(ኢዜአ):- የግብርና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን በማሳካት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ  የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ።

በግብርና ሚኒስቴር የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም እና የኢትዮጵያ አየር ንብረት የሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት የመስክ ተሽከርካሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎችና የውሃ ሞተር ፖምፖችን ለክልሎች የማስረከብ ፕሮግራም ተካሂዷል። 


 

የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ 267 የመስክ ተሽከርካሪዎች፣ 1ሺህ 854 ሞተር ሳይክሎች፣ 2 ሺህ 289 ፓምፖችን ለክልሎች፣ ለሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች እና ለፌዴራል ፈጻሚ ተቋማት  በድጋፍ አስረክበዋል።  


 

ድጋፎች በአጠቃላይ ወደ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ከአጋር አካላት በተገኘ ገንዘብ የተገዙ መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁ ወቅት የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ እንዳሉት፤ የግብርና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን ለማሳካት የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት ያልታረሱ መሬቶችን ወደ ምርት ማስገባት እንዲሁም በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ የማምረት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።  


 

መካናይዜሽንን ማስፋፋት፣ፋይናንስ ተደራሽ በማድረግ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎችም እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። 

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም የገጠሩን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም