በፕሪሚየር ሊጉ ማንችስተር ዩናይትድ ከቦርንማውዝ ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ማንችስተር ዩናይትድ ከቦርንማውዝ ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2018(ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር በማንችስተር ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ መካከል ዛሬ ይካሄዳል።
ጨዋታው ምሽት 5 ሰዓት ላይ በኦልትራፎርድ ስታዲየም ይደረጋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በ25 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ቦርንማውዝ በ20 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ17ኛ ጊዜ ነው።
ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 16 ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ ዘጠኝ ጊዜ ሲያሸንፍ ቦርንማውዝ አራት ጊዜ ድል ቀንቶታል። ሶስት ጊዜ አቻ ወጥተዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በጨዋታዎቹ ላይ 30 ግቦችን ሲያስቆጥር ቦርንማውዝ 18 ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች በነበራቸው የእርስ በእርስ ግንኙነት ቦርንማውዝ ሁለት ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ ማንችስተር ዩናይትድ አንድ ጊዜ አሸንፏል። በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል።
ሁለቱ ቡድኖች በጨዋታው ላይ ተመጣጣኝ ፋክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የ43 ዓመቱ ሳይመን ሁፐር ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።