በኢትዮጵያ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና እና መቀሌ 70 እንደርታ ይጫወታሉ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና እና መቀሌ 70 እንደርታ ይጫወታሉ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሶስተኛ ዙር የመጨረሻ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ቡና እና መቀሌ 70 እንደርታ መካከል ዛሬ ይደረጋል።
የቡድኖቹ ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ ቡና በሁለተኛው ዙር አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ተጋጣሚ መቀሌ 70 እንደርታ በሁለተኛው ዙር ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 በማሸነፍ ሶስተኛውን ዙር መቀላቀሉ ይታወቃል።
ኢትዮጵያ ቡና በፕሪሚየር ሊጉ በ11 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል።
መቀሌ 70 እንደርታ በአምስት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፈው ክለብ ሩብ ፍጻሜ የሚቀላቀል የመጨረሻው ቡድን ይሆናል።
ሁለቱ ክለቦች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ18ኛ ሳምንት ይገናኛሉ።
ሲዳማ ቡና፣ ቤንች ማጂ ቡና፣ መቻል፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ቦዲቲ ከተማ፣ ኢትዮጵያ መድን እና ነጌሌ አርሲ ሌሎች የሩብ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦች ናቸው።