ቀጥታ፡

በሊጉ ተጠባቂ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን አሸንፏል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 5/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በስልኸረስት ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፊል ፎደን ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የጨዋታው ኮከብ ሆኖ የተመረጠው ሃላንድ በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 17 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቱን አጠናክሯል።

በሊጉ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ሲቲ ነጥቡን ወደ 34 ከፍ በማድረግ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ክሪስታል ፓላስ በ26 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች አስቶንቪላ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 2 በማሸነፍ በ33 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ኖቲንግሃም ፎረስት ቶተንሃም ሆትስፐርስን 3 ለ 0፣ ሰንደርላንድ ኒውካስትል ዩናይትድን 1 ለ ዐ አሸንፈዋል።

ብሬንትፎርድ እና ሊድስ ዩናይትድ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

የ16ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር በማንችስተር ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ መካከል ነገ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም