ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ አለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ አለፉ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 5/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሶስተኛ ዙር የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል።
በአዳስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን እና ብሌዝ ናጎ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ንብ እግር ኳስ ክለብን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ያሬድ ከበደ በጨዋታ እና ጌትነት ተስፋዬ በቀለም ቅጣት ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ኢዮብ ደረሰ ለንብ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቶቹን ተከትሎ ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሩብ ፍጻሜ አልፈዋል።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ቤንች ማጂ ቡና ደብረብርሃን ከተማን በመለያ ምት አሸንፎ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።
ኢትዮጵያ መድን፣ መቻል፣ ነጌሌ አርሲ እና ቦዲቲ ከተማ ሌሎች ለሩብ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦች ናቸው።
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር የመጨረሻ መርሃ ግብር ነገ በኢትዮጵያ ቡና እና መቀሌ 70 እንደርታ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ ይደረጋል።