ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ዋንጫ ቤንች ማጂ ቡና ለሩብ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 5/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር ቤንች ማጂ ቡና ደብረብርሃን ከተማን በመለያ ምት አሸንፏል።

በአዳስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቡድኖቹ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ሀይደር ሽኩር ለደብረብርሃን ከተማ፣ መሐመድ ናስር ለቤንች ማጂ ቡና ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቶ ቤንች ማጂ ቡና 5 ለ 4 አሸንፏል።

ቤንች ማጂ ቡና ለሩብ ፍጻሜ ያለፈ አምስተኛ ቡድን ሆኗል።

በአሁኑ ሰዓት ሲዳማ ቡና ከአርባ ምንጭ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከንብ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም