በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 5/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዝናሽ ሰለሞን እና ዘለቃሽ አሰፋ በመጀመሪያ አጋማሽ ባስቆጠሯቸው ግቦች አዳማ ከተማ መሪ ሆኗል።
ከእረፍት መልስ ሲፋን ተስፋዬ በጨዋታ እና ምስር ኢብራሂም በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ ባሰረፏቸው ግቦች አዳማ ከተማ አቻ ሆኗል።
አዳማ ከተማ በ15 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
ድሬዳዋ ከተማ በ13 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ከቀኑ 9 ሰዓት የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።