በኢትዮጵያ ዋንጫ ለሩብ ፍጻሜ የሚያልፉ ክለቦች የሚለዩባቸው ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ለሩብ ፍጻሜ የሚያልፉ ክለቦች የሚለዩባቸው ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 5/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር የሁለተኛ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ደብረብርሃን ከተማ ከቤንች ማጂ ቡና ከቀኑ 7 ሰዓት እና ሲዳማ ቡና ከአርባምንጭ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ ይጫወታሉ።
ሲዳማ ቡና አምና የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ እንደደነበር የሚታወስ ነው።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከንብ እግር ኳስ ክለብ ከቀኑ 7 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ትናንት በተደረጉ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ነጌሌ አርሲ፣ ቦዲቲ ከተማ፣ ኢትዮጵያ መድን እና መቻል ለሩብ ፍጻሜ አልፈዋል።