ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ አርሰናል ዎልቭስን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል  ዎልቭስን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲ በተካሄደው ጨዋታ በ70ኛው ደቂቃ ቡካዮ ሳካ ከማዕዘን ምት ያሻገረውን የዎልቭሱ ግብ ጠባቂ ሳም ጆንስተን በ70ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ አስቆጥሮ አርሰናል መሪ ሆኗል።

ቶሉ አርኮዳሬ በ90ኛው ደቂቃ ዎልቭስን አቻ አድርጓል።

ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ ሲባል ከ11 ወራት በኋላ ከጉዳት የተመለሰው ጋብርኤል ጄሱስ በ94ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ለአርሰናል ወሳኝ ድል አስገኝቷል።

በጨዋታው አርሰናል ብልጫ ወስዶ ቢጫወትም በዎልቭስ የጥልቀት መከላከል የጨዋታ ስልት ፈተና አጋጥሞታል።

በውድድር ዓመቱ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው የሊጉ መሪ አርሰናል ነጥቡን ወደ 36 ከፍ አድርጓል።

ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ ብሏል።

በአንጻሩ በሊጉ 14ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ዎልቭስ በሁለት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።

ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።

በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ነገ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ከሜዳው ውጪ የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም